top of page
logo gojam.png
logogonder.png
logo shewa.png
logowelo.png

የአማራ ሕብረት ለምን አስፈለገ?

የአማራ ህዝብ ለሀገሩ ህልውና እና እድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ቢኖረውም በአለፉት ሃምሳ ዓመታት ተከታታይ የአገዛዝ ሥርዓቶች ከፍተኛ የሆነ የዘር ማጥፋትና ሰብዓዊ ግፍ ተፈጽሞበታል። በስልጣን ላይ ያለው ኦሮሞ መራሽ የብልጽግና ሥርዓት በሁሉም የኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የአማራን በህይወት የመኖር ተፈጥሮዓዊ መብት በከፍተኛ አደጋ ላይ ጥሏል። አማራው በመሰረታት የራሱ ዋና ከተማ አዲስ አበባ እንኳን እንዳይገባ በመከልከል፣ እንዳይሰራ እየታገደ፣ ቤት ንብረቱ እየፈረሰና እየተነጠቀ በመሳደድ ላይ ይገኛል። ይህ በአማራው ላይ የሚፈጸመው ዘርፈ ብዙ ጭካኔ የተሞላበት የመንግሥት አካሄድ ሁሉንም የዘር ማጥፋት መስፈርቶች ያሟላል።

የሥርዓቱ በደል በዚህ ሳይወሰን የአማራን ህዝብ ደብዛ ለማጥፋት በታሪኩ፣ በቋንቋውና በእሴቶቹ ላይ ሁሉ ጦርነት ተከፍቶበታል። በዚህም ምክንያት ዛሬ አማራው ከምንጊዜውም የበለጠ ከባድ የህልውና አደጋ ተጋርጦበታል። የአማራ ህዝብ በአንድነት ሆኖ ራሱን ከባሰ እልቂት ከማዳን በስተቀር ሌላ አማራጭ የለውም።

ይህን የህልውና አደጋ ለመቅረፍ እና አማራው እያደረገ ያለውን የህልውና ትግል ለማገዝ ከአራቱ ክፍላተሀገር የተሰባሰቡ ድርጅቶች፤ ማለትም ጎጃም አለም አቀፍ ትብብር፣ ጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ቤተ አማራ ወሎ አለም ዓቀፍ ማህበር እና ደቂቀ ምኒልክ ዘሸዋ አማራ ማህበር በተከታታይ የጋራ ውይይት ሲያደርጉ ቆይተው የአማራ ክፍላተሀገር ሕብረት በሚል ስያሜ አብሮ ለመሥራት ተስማምተዋል።

የአማራ ክፍላተሀገር ህብረት መመስረት ለአማራ ህዝብ ህልውና መጠበቅ እና እድገት በሚደረገው የጋራ ትግል ወሳኝ ምዕራፍ ነው። ይህ ህብረት የአማራን ህዝብ ርስቱን ለመጠበቅ፣ ሰብዓዊ መብቱን ለማስከበር፣ ራሱን ለመከላከል እና ለመጭው ትውልድ ብሩህ ተስፋን ለመገንባት ቁርጠኝነትን ያሳይል።

አላማችን

የአማራ ህዝብ ለሀገሩ ህልውና እና እድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ቢኖረውም በአለፉት ሃምሳ ዓመታት ተከታታይ የአገዛዝ ሥርዓቶች ከፍተኛ የሆነ የዘር ማጥፋትና ሰብዓዊ ግፍ ተፈጽሞበታል። በስልጣን ላይ ያለው ኦሮሞ መራሽ የብልጽግና ሥርዓት በሁሉም የኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የአማራን በህይወት የመኖር ተፈጥሮዓዊ መብት በከፍተኛ አደጋ ላይ ጥሏል። አማራው በመሰረታት የራሱ ዋና ከተማ አዲስ አበባ እንኳን እንዳይገባ በመከልከል፣ እንዳይሰራ እየታገደ፣ ቤት ንብረቱ እየፈረሰና እየተነጠቀ በመሳደድ ላይ ይገኛል። ይህ በአማራው ላይ የሚፈጸመው ዘርፈ ብዙ ጭካኔ የተሞላበት የመንግሥት አካሄድ ሁሉንም የዘር ማጥፋት መስፈርቶች ያሟላል። የሥርዓቱ በደል በዚህ ሳይወሰን የአማራን ህዝብ ደብዛ ለማጥፋት በታሪኩ፣ በቋንቋውና በእሴቶቹ ላይ ሁሉ ጦርነት ተከፍቶበታል። በዚህም ምክንያት ዛሬ አማራው ከምንጊዜውም የበለጠ ከባድ የህልውና አደጋ ተጋርጦበታል። የአማራ ህዝብ በአንድነት ሆኖ ራሱን ከባሰ እልቂት ከማዳን በስተቀር ሌላ አማራጭ የለውም።

ይህን የህልውና አደጋ ለመቅረፍ እና አማራው እያደረገ ያለውን የህልውና ትግል ለማገዝ ከአራቱ ክፍላተሀገር የተሰባሰቡ ድርጅቶች፤ ማለትም ጎጃም አለም አቀፍ ትብብር፣ ጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ቤተ አማራ ወሎ አለም ዓቀፍ ማህበር እና ደቂቀ ምኒልክ ዘሸዋ አማራ ማህበር በተከታታይ የጋራ ውይይት ሲያደርጉ ቆይተው የአማራ ክፍላተሀገር ሕብረት በሚል ስያሜ አብሮ ለመሥራት ተስማምተዋል።

የአማራ ክፍላተሀገር ህብረት መመስረት ለአማራ ህዝብ ህልውና መጠበቅ እና እድገት በሚደረገው የጋራ ትግል ወሳኝ ምዕራፍ ነው። ይህ ህብረት የአማራን ህዝብ ርስቱን ለመጠበቅ፣ ሰብዓዊ መብቱን ለማስከበር፣ ራሱን ለመከላከል እና ለመጭው ትውልድ ብሩህ ተስፋን ለመገንባት ቁርጠኝነትን ያሳይል።

  • s-facebook
  • Twitter Metallic
  • s-linkedin
bottom of page