እንኳን ደህና መጣችሁ

Welcome to
Union of Amhara Provinces
Uniting Voices for Justice, Culture, and a Stronger Ethiopia

የአማራ ሕብረት ለምን አስፈለገ?
የአማራ ህዝብ ለሀገሩ ህልውና እና እድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ቢኖረውም በአለፉት ሃምሳ ዓመታት ተከታታይ የአገዛዝ ሥርዓቶች ከፍተኛ የሆነ የዘር ማጥፋትና ሰብዓዊ ግፍ ተፈጽሞበታል። በስልጣን ላይ ያለው ኦሮሞ መራሽ የብልጽግና ሥርዓት በሁሉም የኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የአማራን በህይወት የመኖር ተፈጥሮዓዊ መብት በከፍተኛ አደጋ ላይ ጥሏል። አማራው በመሰረታት የራሱ ዋና ከተማ አዲስ አበባ እንኳን እንዳይገባ በመከልከል፣ እንዳይሰራ እየታገደ፣ ቤት ንብረቱ እየፈረሰና እየተነጠቀ በመሳደድ ላይ ይገኛል። ይህ በአማራው ላይ የሚፈጸመው ዘርፈ ብዙ ጭካኔ የተሞላበት የመንግሥት አካሄድ ሁሉንም የዘር ማጥፋት መስፈርቶች ያሟላል። የሥርዓቱ በደል በዚህ ሳይወሰን የአማራን ህዝብ ደብዛ ለማጥፋት በታሪኩ፣ በቋንቋውና በእሴቶቹ ላይ ሁሉ ጦርነት ተከፍቶበታል። በዚህም ምክንያት ዛሬ አማራው ከምንጊዜውም የበለጠ ከባድ የህልውና አደጋ ተጋርጦበታል። የአማራ ህዝብ በአንድነት ሆኖ ራሱን ከባሰ እልቂት ከማዳን በስተቀር ሌላ አማራጭ የለውም።
ይህን የህልውና አደጋ ለመቅረፍ እና አማራው እያደረገ ያለውን የህልውና ትግል ለማገዝ ከአራቱ ክፍላተሀገር የተሰባሰቡ ድርጅቶች፤ ማለትም ጎጃም አለም አቀፍ ትብብር፣ ጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ቤተ አማራ ወሎ አለም ዓቀፍ ማህበር እና ደቂቀ ምኒልክ ዘሸዋ አማራ ማህበር በተከታታይ የጋራ ውይይት ሲያደርጉ ቆይተው የአማራ ክፍላተሀገር ሕብረት በሚል ስያሜ አብሮ ለመሥራት ተስማምተዋል።
የአማራ ክፍላተሀገር ህብረት መመስረት ለአማራ ህዝብ ህልውና መጠበቅ እና እድገት በሚደረገው የጋራ ትግል ወሳኝ ምዕራፍ ነው። ይህ ህብረት የአማራን ህዝብ ርስቱን ለመጠበቅ፣ ሰብዓዊ መብቱን ለማስከበር፣ ራሱን ለመከላከል እና ለመጭው ትውልድ ብሩህ ተስፋን ለመገንባት ቁርጠኝነትን ያሳይል።
የአማራ ህዝብ ለሀገሩ ህልውና እና እድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ቢኖረውም በአለፉት ሃምሳ ዓመታት ተከታታይ የአገዛዝ ሥርዓቶች ከፍተኛ የሆነ የዘር ማጥፋትና ሰብዓዊ ግፍ ተፈጽሞበታል። በስልጣን ላይ ያለው ኦሮሞ መራሽ የብልጽግና ሥርዓት በሁሉም የኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የአማራን በህይወት የመኖር ተፈጥሮዓዊ መብት በከፍተኛ አደጋ ላይ ጥሏል። አማራው በመሰረታት የራሱ ዋና ከተማ አዲስ አበባ እንኳን እንዳይገባ በመከልከል፣ እንዳይሰራ እየታገደ፣ ቤት ንብረቱ እየፈረሰና እየተነጠቀ በመሳደድ ላይ ይገኛል። ይህ በአማራው ላይ የሚፈጸመው ዘርፈ ብዙ ጭካኔ የተሞላበት የመንግሥት አካሄድ ሁሉንም የዘር ማጥፋት መስፈርቶች ያሟላል።
የሥርዓቱ በደል በዚህ ሳይወሰን የአማራን ህዝብ ደብዛ ለማጥፋት በታሪኩ፣ በቋንቋውና በእሴቶቹ ላይ ሁሉ ጦርነት ተከፍቶበታል። በዚህም ምክንያት ዛሬ አማራው ከምንጊዜውም የበለጠ ከባድ የህልውና አደጋ ተጋርጦበታል። የአማራ ህዝብ በአንድነት ሆኖ ራሱን ከባሰ እልቂት ከማዳን በስተቀር ሌላ አማራጭ የለውም።
ይህን የህልውና አደጋ ለመቅረፍ እና አማራው እያደረገ ያለውን የህልውና ትግል ለማገዝ ከአራቱ ክፍላተሀገር የተሰባሰቡ ድርጅቶች፤ ማለትም ጎጃም አለም አቀፍ ትብብር፣ ጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ቤተ አማራ ወሎ አለም ዓቀፍ ማህበር እና ደቂቀ ምኒልክ ዘሸዋ አማራ ማህበር በተከታታይ የጋራ ውይይት ሲያደርጉ ቆይተው የአማራ ክፍላተሀገር ሕብረት በሚል ስያሜ አብሮ ለመሥራት ተስማምተዋል።
የአማራ ክፍላተሀገር ህብረት መመስረት ለአማራ ህዝብ ህልውና መጠበቅ እና እድገት በሚደረገው የጋራ ትግል ወሳኝ ምዕራፍ ነው። ይህ ህብረት የአማራን ህዝብ ርስቱን ለመጠበቅ፣ ሰብዓዊ መብቱን ለማስከበር፣ ራሱን ለመከላከል እና ለመጭው ትውልድ ብሩህ ተስፋን ለመገንባት ቁርጠኝነትን ያሳይል።
አላማችን
ራዕይ
አማራው በመላ ኢትዮጵያ ህልውናው ተረጋጋጦ፣ መብትና ጥቅሙ ተከብሮ፣ ፍትህና ርትዕ አግኝቶ፣ የተዛባ ታሪኩ ተስተካክሎ፣ በማንነቱ ተከብሮ፣ ከሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር እኩል ተከባብሮ፣ የራሱን የውስጥ እድገትና ልማት በራሱ የመወሰን አቅምና መብት ኖሮት፣ በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ሃብቱ ተጠቃሚ ሆኖ፣ ታሪካዊ አፅመ ርስቱና ይዞታው ተመልሶ፣ ማህበራዊ ደህንነቱ ተጠብቆ በዘላቂ እድገት፣ ሠላምና፣ የስልጣኔ ጎዳና ሲራመድ ማየት።
ተልዕኮ
አማራን ማዕከል ያደረጉ የክፍላተሀገር ድርጅቶችን በመቀናጀት ሠፊ ህዝባዊ መሠረት ያለው የትብብር ማዕቀፍ በመመሥረት እና መላ የአማራ ተወላጆችና አደረጃጀቶች የትግሉ ጠንካራ አጋርና ደጀን እንዲሆኑ ማስቻል። አማራው ያለውን እምቅ እውቀትና ፣ ልምድ፣ የሰው ኃይል፣ የፋይናንስ አቅምና ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ የተደቀነበትን የህልውና አደጋ እንዲቀለብስና ለዘላቂ ድል እና ሠላም እንዲበቃ ሁለገብ ድጋፍ ማድረግ።